የምርመራ ጋዜጠኝነት ዘዴዎች ትርጓሜ

የምርመራ አዘጋገብን በሚመለከት የተለያዩ ትርጓሜዎች ይሰጡ እንጂ፣ አዘጋገቡ በሚያካትታቸው ነጥቦች ዙሪያ ግን የጋዜጠኝነት ባለሞያዎች ልዩነት የላቸውም። ይልቁንም ሥልታዊ፣ ጥልቀት ያለው፣ ያልተቀዳ ጥናትና ዘገባ፣ ብዙ ጊዜ በምስጢር የተያዙ ጉዳዮችን የሚያጋልጥ ነው በሚለው ላይ ይስማማሉ። ሌሎች ደግሞ ተግባራዊነቱ ላይ የሕዝብ የሆኑ መዝገቦችንና መረጃዎችን በከፍተኛ ደረጃ አካትቶ አትኩሮቱ ማኅበራዊ ፍትህና ተጠያቂነት እንደሆነ አጽንዖት ይሰጣሉ።

ጠቃሚ ምክሮች ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ ለሚዘግቡ ጋዜጠኞች

አዲስ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ የዓለማችን ትልቁ ዜና ሆኖ ቀጥሏል። እንደ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ እስከ አሁን የኮሮና ቫይረስ ከ167 በላይ የዓለም አገራትን አዳርሶ፣ 11 ሺሕ በላይ ሰዎችን ገድሏል። ከ286 ሺሕ በላይ ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተይዘዋል።

በአፍሪካ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ፡ እርዳታ እና ድጋፎች

የምርመራ ዘገባ ሥራ ሁልጊዜም ውድ ነው። ዘርፉ በዓለም ደረጃ በከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ በገባበት በዚህ ጊዜ፣ በርካታ የሚባሉ የንግድ//ኮሜርሻል ሚድያዎች ግንዘብን እንደወትሮው ለምርመራ ዘገባ አይመድቡም።

በአፍሪካ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ፡ ፀጥታና ደኅንነት በአፍሪካ

በተፈጥሮው፣ የምርመራ ጋዜጠኝነት አደገኛ ሲሆን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ዘጋቢዎችና ኤዲሪተሮችን ስጋት ላይ ይጥላል። ሙሰኛ የሆኑና እጃቸው የዘረመ የመንግሥት ባለሥልጣናት ቆሻሻ የሚያወጡ ጋዜጠኞች ማስፈራሪያዎ ይገጥሟቸዋል። ይህም የምርመራ ሥራውን ለማስቆም የሚድያ ተቋማቸውን እስከመጨረሻው ዝም እስከማሰኘት የሚደርስ ጥረት ነው። እነዚህን ጋዜጠኞች ከደኅንነት እና ፀጥታ ስጋት ለመጠበቅ፣ አንዳንድ የአፍሪካ እና ዓለማቀፍ ድርጅቶች፣ በተመረጡ የአፍሪካ አገራትም ሆነ በመላው አኅጉሪቱ፣ ችግር ላይ ላሉ ምስጢር አጋላጭ ጋዜጠኞች ድጋፍ የሚያቀርቡበትን ፕሮግራም ሠርተዋል።

የናይጄሪያው ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR) በኮቪድ 19 ምላሽ ተጠሪነትን ለመፍጠር እያደረገ ያለው ግፊት

መቀመጫውን በናይጄሪያ ያደረገ ለትርፍ ያተቋቋመው የናይጄሪያ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ማእከል (ICIR)፣ አሁን ላይ ሽፋኑንም አገሪቱ ለኮቪድ 19 እየሰጠች ባለችው ምላሾች ዙሪያ አድርጓል። በዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ (GIJN) የአፍሪካ ኤዲተር ከሆነው ከቤኖን ኸርበርት ኦሉካ ጋር ቆይታ ያደረገው ዳዮ አይታን ስለ ቡድኑ እንቅስቃሴ እንዲሁም ለአፍሪካ ስጋት በሆነው ወረርሽኙ ዙሪያ የምርመር ዘገባ መሥራትን በሚመለከት አንስቷል። ዳዮ አይታን የምርመራ ዘጋቢ፣ የዜና ክፍል አማካሪና የሚድያ አሠልጣኝ ነው።

የአፍሪካ ዓለማቀፍ የምርመራ ዘገባ ኔትወርክ (GIJN): የሕዝብ መረጃ መዛግብት ተደራሽነት

በሰብ ሰሃራ አፍሪካ በሚገኙ በርካታ አገራት፣ አሁን ድረስ መረጃና የሕዝብ የሆኑ የመረጃ መዛግብትን ማግኘት ፈታኝና ከባድ ሥራ ነው። ለምን ቢባል ጋዜጠኞች መረጃ ሲጠይቁ የሚደግፋቸውና የመንግሥት ባለሥልጣናት የሕዝብ የሆኑ መረጃዎችን እንዲሰጡ ግድ የሚላቸው ሕግ አለመኖሩ ነው።

የምርመራ ጋዜጠኝነት መመሪያዎች

ጠቃሚ ነጥቦች፣ መሣሪያዎችና ተጨማሪ ሥልጠናዎችን እየፈለጉ ነው? ከታች የሚታዩት መመሪያዎች የምርመራ ጋዜጠኝነት ላይ ያተኮሩ ሲሆን፣ ከተለያዩ የዓለም አገራት የተውጣጡ ተጨባጭ ጥናቶችን እና ምሳሌዎችን ያቀርባሉ። አብዛኞቹ በነጻ የሚገኙ ናቸው፣ ክፍያ አላቸው ተብለው ከተጠቀሱት ውጪ።

የኦንላይን የምርምር መሣሪያዎች/

በቢቢሲ ቁጥር አንድ በሚለው የኦንላይን መርማሪው ፖል ማየርስ የቀረበው ኦንላይን የጥናት መሣሪያዎችና የምርመራ ዘዴዎች ለዓለማቀፍ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኔትወርክ አንባቢዎች የኦንላይን የጥናት ፍለጋዎች መነሻ ሆኖ አገልግሏል። ይህ የእርሱ ‹ሪሰርች ክሊኒክ› የተባለ ድረገጽ፣ የብዙ ጥናታዊ ሥራዎች ሊንክ እና የ‹ጥናት ግብዓቶች› ይገኙበታል።

ማየርስ በ2019 የኔትወርኩ ዌብናር ላይ ሰዎችን ኦንላይን እንዴት እናገኛለን ለሚለው ጠቃሚ ምክሮችን አቅርቧል። የዓለማቀፉ ኔትወርክ ማየርስን ያቀረበውን በጽሑፍ አሰናድቶ ነበር። አራት ጥያቄዎች፣ በኦንላይን ምርጡ መርማሪ ፓውል ማየርስ።

እዚህ ላይ ‹gijn.org› ላይ የሚገኙ የማየርስን ሌሎች መመሪያዎች ተመልከቱ፤

ትዊተርን በመጠቀም ሰበር ዜና በሚገኙባው ቦታዎች የነበሩ ሰዎችን ለማግኘት

ለድረገጽ መፈለጊያ ብራውዘርን በቅርብ ማስቀመጥ፣

ወደኋላ ተመልሶ ማሰስ

‹ኦንላይን ፍለጋና ቁልፍ የመረጃ ቋት› በሚል ከዚህ ጋር በተያያዘ ለተዘጋጀ ቪድዮ፣ የኔትወርኩን የዩትዩብ ቻናል ይመልከቱየዓለማቀፍ የምርመራ ጋዜጠኝነት ኔትወርክ የምርመራ መሣሪያዎች መገኛ (Toolbox)፣ በኔትወርኩ አባል አላስታየር ኦቴር የተዘጋጀ አንድ ጽሑፍ፣ የተመረጡ ርእሰ ጉዳዮችን ይቃኛል፤

ስሞችን እና ድረገጾችን መፈለግ፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ማረጋገጥ፣ የመፈለጊያዎች ክምችት
ሰዎች መፈለግ፣ ድሮችን መበርበርና ራስን ደኅና ጠብቆ ማቆየት
ለሰዎችና ኩባንያዎች የኋላ መነሻ መስጠት
ትዊተርን መበርበርና የድረገጾች አዲስ መረጃ መከታተል
ከመረጃ ትንታኔ ባሻገር ድረገጽ ላይ በጥልቀት መፈለግ

ጄክ ክሪፕስ በብሎጉ ላይ በቋሚነት ጠቃሚ ነጥቦችን ያጋራል። osintpodcast.com ላይ በሚገኝ ፖድካስት ላይ አስተዋዋቂ ነው። በሕዝብና የግል ዘርፉ ላይ ልምድ ያለው የወል/የሕዝብ የሆኑ የመረጃ ምንጮች ኢንተለጀንስ ተንታኝ ነው።

OSINTcurio.us ሳምንታዊ ፖድካስቶችን፣ ዌብካስቶችና ለዐስር ደቂቃ የሚያቀርቡ ጠቃሚ ነጥቦችን በተንቀሳቃሽ ምስል ያቀርባል። በዚህም የተለያዩ የወል ምንጭ የምርመራ መንገዶችን ይሸፍናል። ይህም የማኅበረሰብ ፕሮጀክት ሲሆን፣ በ2018 መጨረሻ አካባቢ በዐስር አቅራቢ ባለሞያዎች የተጀመረ ነው።

Sector035, <Just a shadowy nerd> በሚል ቅጥያ የሚጠራ ሲሆን፣ በየሳምንቱ ጠቃሚ ነጥቦችን ያቀርባል። በተለይም የመልክዓ ምድራዊ መገኛን በሚመለከት። Week in OSINT እና Quiztimeን ያሳትማል።

የአንድን ሰው ማን፣ ከየት እና መቼ የሚሉ ጉዳዮች የሚመረምር የኦንላይን ዘዴ። ይህም ሌላው በኢንተርኔት መፈለጊያ ዝርዝር ባለሞያ በሆነው ሔንክ ቫን ኤስ የተዘጋጀ ነው። ማን ምን ፖስት አደረገ፣ (Who Posted What) የሚለውንም ተመልከቱ። ይህም የቫን ኢስ ሐሳብ ሆኖ፣ በዳንኤል ኤንድሬስ የዳበረ ሲሆን፣ በፌስቡክ ገጽ ላይ ቁልፍ የሆነውን አንድ ቃል በማስገባት፣ በተወሰነ ጊዜ ወይም በተሰጡ ጊዜያት መካከል ፖስት የተደረጉ ተመሳሳይ ቁልፍ ቃላትን የሚፈልግ ነው።

የወል/ሕዝብ መረጃ ምንጮች ኢንተለጀንስ ማዕቀፍ የተብራራ እና በየጊዜው የሚጨምሩ ለምርመራ ሥራ የሚያገለግሉ የዲጂታል መሣሪያዎች ዝርዝር የያዘ ነው።

ውስብስብ የሆነ ድርን በጥልቀት መመርመር፣ በጄኒና ሴግኒኒ፤ ውስብስብ ለሆኑ የጎግል ማሰሻዎች የሚረዱና የተሻሻሉ ጠቃሚ ነጥቦች በመጥቀስ ይጀምራል። በዚህ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የመረጃ ጋዜጠኝነት ፕሮግራም የጋዜጠኝነት ትምህርት ዳይሬክተር የቀረበ ገለጻ፣ ጉግል እንደ ድልድይ በመጠቀም ለምሳሌ የአደገኛ እጽ ዝውውርን በሚመለከት ድሮችን በጥልቀት ወደ መመርመር ተሻግሯል።

እንዴት የድር ጥልቅ መርማሪ መሆን እንደሚቻል. ይህ የግሎባል የምርመራ ጋዜጠኝነት ኔትወርክ ጽሑፍ፣ በጀርመናዊው ጋዜጠኛ፣ ተመራማሪና በ11ኛው የግሎባል የምርመራ ጋዜጠኝነት ኮንፈረንስ አሠልጣኝ፣ በአልብሬት ኡዴ የተሰጠውን ምክር ያብራራል። ኡዴ እንደሚለው፣ የማሰሻ ማንቀሳቀሻዎች በድር ላይ ጥልቅ ምርመራ ለማድረግ ምንም የሚሰጡት ዋጋ የለም። እናም የእርሱ ምክር በተለየ መንገድ ማሰብ የሚል ሲሆን፣ ተጨማሪ ነጥቦችንም አክሏል። ተያያዥ ብሎ ያሰፈራቸውን ጠቃሚ ነጥቦች በዚህ ተመልከቱ፤ ዳታቤዝን መፈለግና መጠቀም (Finding and using databases) 

የተሻሉ/የረቀቁ የጎግል ማሰሻዎች/መፈለጊያዎች

የጎግልን የረቀቁ የመፈለጊያ ገጽ እና የመፈለጊያውን መመሪያዎችን መጠቀም። በተያያዘ ጎግል የመፈለጊያ ትምህርቶችን ጨምሮ ‹ፓወር ሰርቺንግ› ኮርሶችን እና ሌሎችንም በሚመለከት ለጋዜጠኞች ሥልጠና ይሰጣል።

ቁልፍ ለሆኑ የመመሪያዎች ዝርዝር፣ በፖል ማየርስ የተዘጋጀውን ‹Google’s Advanced Search Syntax› ይመልከቱ፤

መሠረታዊ ጉዳዮችን ለማወቅ በ‹ኤክስፐርቲዝፋይንደር› የተዘጋጀውን ‹Google Search Tips for Journalists› ይመልከቱ፤

ከዛም ተከታዮቹን ሞክሩ፣

የዳንኤል ረስል የመፈለጊያ ጥናት እና የእርሱ የጉግል የረቀቁ የመፈለጊያ ኦፕሬተሮች

ኮፎርጅ ከተባለው የአይቲ ኩባንያ ኤሪክ ሜሊሉ ያዘጋጀው፣ ምርጥ ለሚባል ኀሰሳ የሚረዱ 37 የረቀቁ የጎግል መፈለጊያ ጠቃሚ ነጥቦች

ከኦቤርሎ ኩባንያ በዴቪድ ቭራኒካር የተዘጋጀ፣ የጎግል የረቀቁ መፈለጊያዎች፣ ለተሻሉ ፍለጋዎች ጠቃሚ ነጥቦችና አሠራሮች

ኪ-ወርድ ቱል ከተባለ ብሎግ የተገኘ፣ ጎግል የረቀቀ መፈለጊያ፣ የተሻለ መረጃ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል (2 እጥፍ የሚፈጥን)

የጉግል መፈለጊያ ኦፕሬተሮች፤ ሙሉ ዝርዝሮች (42 የረቀቁ ኦፕሬተሮች) በጆሹዋ ሀርድዊክ

ከሳን አንቶኒዮ ቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ ቤተመጻሕፍት የተገኘ፣ የረቀቀ የጎግል መፈለጊያ

የኤዮጋን ስዌኒ የፈጠራ ውጤት የሆነው ‹OSINT Essentials›፣ ለኦንላይን ማጣራት ሥራዎች፣ ለዲጂታል ጋዜጠኝነት እና ለወል የመረጃ ምንጭ ኢንተለጀንስ ሥራ የሚጠቅሙ፣ ነጻ መሣሪያዎችና አገልግሎቶችን ማግኛ ሊንኮችን የሚያቀርብ ነው።

‹First Draft› ዓለማቀፍ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ የተሻሉ ጠቃሚ መሣሪያዎችን ሰብስቦ በመያዝ ጋዜጠኞችን የሚደግፍ ነው። በተያያዘ ‹First Draft’s Essential Guide to Verifying Online Information› (2019) በሚል ርዕስ የሚገኝ የፒዲኤፍ ሰነድና ተያያዥ የሥልጠና ግብዓቶችን ማየት ይቻላል፤

በደቡብ አፍሪካ ጋዜጠኛና አሠልጣኝ ሬይሞንድ ጆሴፍ የተዘጋጀ፤ መሣሪያዎች፣ ጠቃሚ ሊንኮችና ግብዓቶች፤ በትዊተር፣ ማኅበራዊ ሚድያ፣ ማጣሪያ፣ ዶሜይን እና የአይፒ መረጃ፣ ዓለማቀፍ የስልክ ደብተሮች እና ሌሎችም ላይ የሚገኝ የመረጃ ገጽ ነው። ጆሴፍ በሰጠው ገለጻም፣ እንዴት የዲጂታል መርማሪ መሆን ይቻላል የሚለውን አብራርቷል።

የማይታየውን ማጋለጥ፣ (Exposing the Invisible) በገጹ የተለያዩ መመሪያዎች ያሉት ሲሆን፣ ‹ጎግል ዶርኪንግ›ን ያካትታል። ብዙኀን በሚጠቀሙባቸው ድረገጾች የተደበቁ መረጃዎችን እና የኅብረሰተብ በሆኑ ሰርቨሮች ያሉ የተጋለጡ ክፍተቶችን በሚመለከት መፈለጊያዎችን መረጃ መጠየቂያ ዘዴ ነው።

በፋይናንሻል ታይምስ ከፍተኛ የዜና ክፍል ባለሞያ የሆነው ማክስ ሐርሎስ ያዘጋጀው፣ መመሪያው ምን ያህል እንደሚያስኬድህ በሚገባ ማወቅ የሚለውን በሚመለከት ገለጻ አድርጓል። የሚቻለው የትኛው ነው?

የኮቪድ 19፡ የምርመራ ዘገባ አንጻሮችን በሚመለከት የባለሞያዎች ምክረ ሐሳብ

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመቋቋም በሚሰጥ ግብረ መልስ በሚወሰድ ከተለመደው ለየት ያለ እርምጃ ጋር በተገናኘ፣ የምርመራ ጋዜጠኞች ሥልጣንን ያለአግባብ መጠቀምና የተጋላጮችን ብዝበዛ የማጋለጥ ሥራቸው ከዚህ በላይ አስፈላጊ ሆኖ አያውቅም። በፍጥነት እየተከሰተ ያለውን ቀውስ ተከትሎ፣ የምርመራ ጋዜጠኞች ትኩረታቸውን ምን ላይ ማድረግ አለባቸው? እንዲሁም ምን ዓይነት መሣሪያዎችን እና ዘዴዎችን መጠቀም ነው ለኮቪድ 19 ምርመራ ዘገባ ወሳኝ የሚሆነው?